0% found this document useful (0 votes)
27 views35 pages

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ግቦች

The document is a strategic plan for the College of Health Sciences at Bahir Dar University for the year 2015. It outlines the college's strengths, weaknesses, opportunities and threats from the previous year. It then discusses objectives for the upcoming year related to improving student success, strengthening health services management, expanding e-learning, and mainstreaming cross-cutting issues. The plan identifies priority areas like improving the teaching-learning process, building research capacity, and enhancing community outreach. It concludes by setting out the college's goals and targets for 2015 under each of the identified priority areas.
Copyright
© All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as DOCX, PDF, TXT or read online on Scribd
0% found this document useful (0 votes)
27 views35 pages

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ግቦች

The document is a strategic plan for the College of Health Sciences at Bahir Dar University for the year 2015. It outlines the college's strengths, weaknesses, opportunities and threats from the previous year. It then discusses objectives for the upcoming year related to improving student success, strengthening health services management, expanding e-learning, and mainstreaming cross-cutting issues. The plan identifies priority areas like improving the teaching-learning process, building research capacity, and enhancing community outreach. It concludes by setting out the college's goals and targets for 2015 under each of the identified priority areas.
Copyright
© All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as DOCX, PDF, TXT or read online on Scribd

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከ.መቆ.

ዳይሬክቶሬት

የ 2015 በጀት ዓመት ዕቅድ

ሰኔ 2014 ዓ.ም

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ርዕስ ገጽ
1.መግቢያ........................................................................................................................5
2.የዳሮክቶሬቱ ጥንካሬዎች/ክፍተቶች/መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች (SWOT Analysis)........7
2.1 የዳይሮክቶሬቱ ጥንካሬ በ 2014 ዓ.ም በጀት ዓመት..............................................................................7
2.2 የዳይሬክቶሬቱ ክፍተት በ 2014 በጀት ዓመት.....................................................................................7
2.3 የዳይሮክቶሬቱ መልካም አጋጣሚዎች...............................................................................................7
2.4 የዳይሬክቶሬቱ በ 2014 ዓ.ም የነበሩ ተግዳሮቶች.................................................................................8
3.የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከ.መቆ ዳይሬክቶሬት የ 2014 ዓ.ም ዋና ዋና ተግባራት
አፈፃፀም ግምገማ................................................................................................................9
3.1 የተገልጋይ እርካታ ከማሳደግ አንጻር የተሰሩ ስራዎች የሁኔታ ግምገማ........................................................9
3.2.የሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ከማሻሻል አንጻር የተሰሩ ስራዎችየሁኔታ ግምገማ................9
3.3 .በ 2014 ዓ.ም ድጋፍና እንክብካቤ ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ስራዎች የሁኔታ ግምገማ..................................9
3.4. በ 2014 ዓ.ም ኤች አይቪን ከመቆጣጠር አንጻር የተሰሩ ተግባራት የሁኔታ ግምገማ...................................10
3.5 . በ 2014 ዓ. ም ኤች.አይ.ቪን ከመከላከል አንጻር የተሰሩ ተግባራት የሁኔታ ግምገማ..................................10
3.6. በ 2014 ዓ.ም የለዉጥ መሳሪያዎችን ከማስፈጸም አኳያ የተሰሩ ስራዎች የሁኔታ ግምገማ.............................11
4. በዳይሮክቶሬቱ አገልግሎቱን የሚያገኙ ደንበኞች....................................................................11
5. የዳይሮክቶሬቱ ዋና ዋና አጋር አካላት..................................................................................11
6. የሁኔታ ማጠቃለያ.........................................................................................................17
7. የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች እና መሪ ቃል.............................................................17
7.1.ተልዕኮ....................................................................................................................................17
7.2.ራዕይ......................................................................................................................................17
7.3.እሴቶች...................................................................................................................................17
7.4.መሪ ቃል.................................................................................................................................18
8. የ 2014 በጀት ዓመት እቅድ መነሻዎች................................................................................18
9.የዳይሬክቶሬቱ የትኩረት መስኮች.......................................................................................18
10. የ 2015 ዓ.ም ግብዓት ማሟላትና ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አፈፃጸም........................................18
10.1. ከአመለካከት ግንባታ አንፃር የተሰሩ ስራዎች..................................................................................18
10.2. ግብዓት ማሟላት....................................................................................................................19
11.የዩኒቨርስቲዉ የአስር ዓመት ስትራቴጂካዊ እቅድ ለማሳካት በዳይሬክቶሬቱ የተወሰዱ ግቦች..............19
ግብ 6.የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ........................................................................................................19
ግብ 8. የሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ማሻሻል...............................................................19
ግብ 9.ዘርፈብዙ ተግባራትን አካቶ (Mainstreaming) መስራት የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር መፍጠርና
ማጠናከር......................................................................................................................................19
ግብ 7.ተቋማዊ አመራርን፣ አመለካከትን፣ አደረጃጀትንና አሰራሮችን ማሻሻል..................................................19
ግብ 1.የትምህርት ጥራት፤አግባብነት እና ተደራሽትን ማረጋገጥ....................................................................19
12.የዳይሬክቶሬቱ የ 2015 በጀት አመት ግቦች.........................................................................19
ግብ 6.1 የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ.....................................................................................................20
ግብ 6.2 የሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ማሳደግ..............................................................20
ግብ-3፡ የድጋፍ እንክብካቤ አገልግሎትን ማሻሻል....................................................................................20
ግብ 6.4 ኤችአይቪ/ኤድስን ለመቆጣጠር የኤች አይቪ/ኤድስን አገልግሎቶችን (Biomedical intervention)
ማስፋፋት......................................................................................................................................20
ግብ 6.5 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስንለመከለከል.ኤች.አይ.ቪን ና በተያያዥ ችግሮች ዙሪያ ያለዉን ግንዛቤ ማሳደግ
(Beheveral intervention.............................................................................................................20
ግብ 6.6 ተቋማዊ አመራርን፣ አመለካከትን፣ አደረጃጀትንና አሰራሮችን ማሻሻል................................................20
ግብ 6.7 ዘርፈብዙ ተግባራትን አካቶ (Mainstreaming) መስራት የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር መፍጠርና
ማጠናከር......................................................................................................................................20
13. የግቦች የአፈጻፀም አቅጣጫ...........................................................................................20
ግብ 6.1.የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ.....................................................................................................22
ግብ 6.2.ሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት በማሻሻል ለሚደገፉ ወገኖች ድጋፍን ማሳደግ.................23
ግብ 6. 3 የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎትን ማሻሻል.................................................................................25
ግብ 6.4 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመቆጣጠር የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን አገልግሎቶችን ( Biomedical intervention)
ማስፋፋት......................................................................................................................................28
ግብ 6.5 ዘርፈብዙ ተግባራትን አካቶ (Mainstreaming) መስራት የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር መፍጠርና
ማጠናከር......................................................................................................................................31
ግብ 6.6 ተቋማዊ አመራርን፣ አመለካከትን፣ አደረጃጀትንና አሰራሮችን ማሻሻል................................................33
ግብ 6.7 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከለከል ኤች.አይ.ቪን እና በተያያዥ ችግሮች ዙሪያ ያለዉን ግንዛቤ ማሳደግ
(Beheveral intervention)...........................................................................................................37
14. ከላይ የተጠቀሱት ስራዎች በመሰራታቸው የሚጠበቁ ውጤቶች...............................................42
15. ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች..........................................................................................42
16.የመፍትሄ አቅጣጫዎች..................................................................................................43
17.የግንኙነት አግባብ........................................................................................................43
18. ማጠቃለያ................................................................................................................43
1.መግቢያ
ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የሰው ልጅ እስካሁን ካጋጠማቸው እጅግ አስከፊ በሽታዎች አንዱ ነው ፡፡ በ 1981

እ.ኤ.አ.ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲታወቅ ከፍተኛ የሆነ የጤና ቀውስ አስከትሏል ፡፡

በዓለም ዙሪያ ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ እስከ 77.3 ሚሊዮን ሰዎች በኤች አይ ቪ እንደ ተያዙ እና 35.4

ሚሊዮን የሚሆኑት ሰወች ደግሞ ከኤድስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች እንደሞቱ ይገመታል ፡፡ በአሁኑ ግዜ

36.9 ሚሊዮን ሰዎች ከኤች አይ ቪ ጋር ይኖራሉ ፡፡ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ግንባር

ቀደም የችግሩ ተቋዳሾች ናቸው ፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራቸንም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ እንደመሆኗ መጠን ከ 1984 እ.ኤ.አ

የመጀመሪው በኤች.አይ.ቪ የተያዘ ሰው ከተገኘ ጀምሮ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ከሆኑት አገራት ተርታ

ተሰልፋለች፡፡

በ 2019 እ.ኤ.አ. በኤች አይ ቪ ዙሪያ በተደረጉ ጥናቶች እና ትንበያዎች ፣በኢትዮጵያ ውስጥ በበሽታው

የተያዙ እና ከኤድስ ጋር በተዛመዱ በሽታወች የሞቱ ሰወች ቁጥር በቅደም ተከተል 606,933 እና 12,146

ናቸው ፡፡
በኢትዮጵያ ዲሞግራፊክ እና የጤና ጥናት (ኢዲ.ኤች.ኤስ) 2016 ሪፖርት ፣ ብሔራዊ የኤች አይ ቪ

ስርጭት 0.9% የደረሰ ሲሆን በተለያዩ ቡድኖች እና በአገሪቱ መልክዓ ምድራዊ አካባቢዎች ልዩነት ነበር ፡፡

ሴቶች እና ወንዶች መካከል ያለውን የስርጭት መጠን ስንመለከት ሴቶች በኤች .አይ ቪ የመያዝ

እድላቸው ከወንዶች የበለጠ መሆኑን ያሳያል (1.2% እና 0.6%) እንዲሁም በከተማ እና ገጠር ነዋሪዎች

መካከል ያለውን ልዩነት ስንመለከት የከተማ ነዋሪዎች ከገጠር ነዋሪዎች በበለጠ ለቫይረሱ ተጋላጭ ሁነው

እናገኛቸዋለን (2.9% ከ 0.4%) ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወረርሽኝ ስጋት ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ

ክፍሎች (ኬ.ፒ.ፒ.) ማለትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፡በከፍተኛ ትምህርት ተቋም

ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች እንዲሁም ሴተኛ አዳሪዎች እና የረጅም እርቀት አሽከርካሪዎች ውስጥ

አሁንም ከፍተኛ ነው ፡፡

ካላይ ባየነው ጥናት መሰረት ዩኒቨርስቲዎች ለቫይረሱ ተጋጭ የሆኑ ወጣት ተማሪዎች እና ሰራተኞች

በብዛት የሚገኙበት ተቋም እንደ መሆኑ መጠን

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ/መቆ ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርስቲዉን ግቦች መሰረት በማድረግ

የራሱን ራዕይ ቀርፆ እና ለራዕዩ ስኬት የሚያግዙ ተግባራትን አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል::

በመሆኑም ዩኒቨርስቲዉ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የተማሪዎችን የመምህራን እና የሰራተኞን ጤንነት

በሀገራችን ብሎም በአለም ላይ የልማት እንቅፋት የሆነዉን ኤች አይ ቪ/ኤድስን በመከላከል እና

በመቆጣጠር በአጠቃላይ የማህረሰቡን ጤንነት በመጠበቅ ዩኒቨርስቲዉ ያቀደዉን ራዕይ በተጨባጭ እዉን

የሚያደርጉ ጤናማ እና ንቁ ሀገር ተርካቢ ዜጋ ለማፍራት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል::

በሐገር አቀፍ ስትራቴጅክ ፕላን ላይ እንደተመለከተው ከ 2021-2025 እ.ኤ.አ ከኤች.አይ.ቪ ነጻ የሆነ ትው


ልድ የመፍጠር ራዕይን ለማሳካት ፤

 95% ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የሚገኝባቸዉ ወገኖች ተመርምረዉ ዉጤታቸዉን እንዲያዉቁ፤


 95% የኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ወገኖችን የፀረ-የኤች.አይ.ቪ ሕክምና ማ
ስጀመር፤
 95% የፀረ-የኤች.አይ.ቪ ሕክምና ውስጥ ያሉ ወገኖችን የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መጠን በሚ
ፈለገው ደረጃ መቀነስ
በመሆኑም የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከ/መቆ ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እና

ሰራተኞች ጤናቸው ተጠብቆ ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን ሐላፊነት በብቃት እንዲዎጡ ለማስቻል

ራሳቸውን ለኤች.አይ.ቪ ከሚያጋልጡ ነገሮች ማለትም ከአደንዛዥ እጽ፣አልኮል መጠጥ እንዲሁም ከአቻ
ግፊት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማስቻል እና ስለ ኤች.አይ.ቪ ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ የቫይረሱን

ስርጭትም ለመቀነስ እና ለመከላከል ለ 2015 በጀት ዓመት በዩኒቨርስቲው ከታቀዱት ስትራቴጂካዊ ግቦች

አኳያ ስራዎችን በማከናወን ዉጤት ለማስመዝገብ ዳይሬክቶሬቱ የራሱን የ 2015 ዓመታዊ ዓቅድ

እንደሚከተለው አቅዷል::

2.የዳሮክቶሬቱ ጥንካሬዎች/ክፍተቶች/መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች


(SWOT Analysis)

2.1 የዳይሮክቶሬቱ ጥንካሬ በ 2014 ዓ.ም በጀት ዓመት


 ምንም እንኳን በሀገራችን በተከሰተው ወቅታዊ ችግር ምክንያት ትምህርት በተደጋጋሚ

ቢቋረጥም ተማሪዎች በተገኙበት አጋጣሚ ሁሉ ስራን በሚገባ በመስራት ጥሩ ውጤት

ማስመዝገብ ችለናል፡፡
 እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ምግብ መድሀኒት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን ባህር ዳር ቅርንጫፍ ሲሰጥ
የነበረው የጸረሱስ ስልጠና ቢቋረጥም ያሉንን ባለሙያዎች በመጠቀም ከ 500 በላይ ተጋላጭ የመነሻ ሀሳብ
በማቅረብ በችግሩ ዙሪያ ተማሪዎችን ተወያይተዋል፡፡

 የጸረ ሱስ ስልጠና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል በተደረገላቸው ድጋፍ አምስት ተማሪዎች

ከነበረባቸው የሱስ ችግር መላቀቅ ችለዋል፡፡

 በዕቅድ ያልተያዙ ስራወችንም መስራት ከአቀድነው በላይ ማስመዝገብ ችለናል፡፡ ለምሳሌ 17

መምህራንን እና የዳይሬክቶሬቱን ባለሙያወች የአቻ ለአቻ የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT)

ማሰልጠን ተችሏል፡፡

 ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት መቻላችን፡፡

2.2 የዳይሬክቶሬቱ ክፍተት በ 2014 በጀት ዓመት


 የዩኒቨርስቲው አመራር፣ መምህራንና ሰራተኞች ለችግሩ ትኩረት አለመስጠታቸዉን መነሻ በማድረግ አዲስ
ስልት በመቅረጽ በስፋት አለመንቀሳቀስ፣

 የዩኒቨርስቲው አመራር፣ መምህራንና ሰራተኞችን ለችግሩ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል


ስልት በመንደፍ በስፋት አለመንቀሳቀስ፣
 በየደረጃው ያለው አመራሮች የኤች አይ ቪ/ኤድስን ና ስነ-ተዋልዶ ጤናን ጉዳይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት
ውስጥ ያስገባና በዋና እቅዱ ውስጥ አካቶ ማቀድ፣ መከታተልና ግብረ መልስ መስጠት እና መምራት
እንዲያስችል ሆኖ እቅዶች አለመታቀዳቸዉ፡፡

2.3 የዳይሮክቶሬቱ መልካም አጋጣሚዎች


 የክልሉ ጤና ቢሮ እና የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ለስራችን ድጋፍ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸዉ፣

 እንዲሁም የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዙሪያ ለመስራት ከበፊቱ የተሻለ
ቁርጠኝነት ማሳየታቸው፣ለምሳሌ-------------

 ዩኒቨርስቲዉ መምህራንን እና የዳይሬክቶሬቱን ሰራተኞች በአቻ ለአቻ የአሰልጣኞች ስልጠና


(TOT) በማሰልጠኑ የአቻ ለአቻ አሰልጣኝ ችግርን መቅረፍ ችለናል፡፡

 I CARE FOR THE NATION ከተባለ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅች ጋር በጋራ በመስራታችን
140 ለችግር የተጋለጡ ሴት ተማሪዎችን የኮፒ አገልግሎት እና የገንዘብ ድጋፍ አግኝተዋል፡፡

2.4 የዳይሬክቶሬቱ በ 2014 ዓ.ም የነበሩ ተግዳሮቶች


 ባለዉ በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት ጉዳይ እና የተጣበበ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ስለነበር
ተማሪዎችን ለማግኘት አዳጋች አድርጎብናል፣

 በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮንዶም እጥረት በማጋጠሙ የተነሳ ድጋፍ ሲያደርጉልን የነበሩ ተቋማት
የኮንደም ድጋፍ ማቋረጣቸው፣

 በኢትዮጵያ ምግብ መድሀኒት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን ባህር ዳር ቅርንጫፍ በጸረ ሱስ ዙሪያ
ተጋላጭ ለሆኑ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በወቅታዊ የሀገራችን ችግር የተነሳ መቋረጡ፣

 በፔዳ ግቢ የመረጃ ማእከል ሰራተኛ አለመኖር፣

 አብዛኛዉ ስራችን ተማሪዎች ላይ እንደሆነ ይታዎቃል። ከተማሪዎቹ ጋር መገናኘት የምንችለዉ


ደግሞ ከትምህርት ነጻ በሚሆኑበት ጊዜ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ምሽት ላይ ከ 11፡00
በኋላ ብቻ በመሆኑ ከመደበኛ የስራ ስዓት ዉጭ በእረፍት ስዓታችን ለመስራት እንገደዳለን፡፡
ለዚህም ደግሞ ትርፍ ስዓት ክፍያ ይቅርና ትራንስፖርት እንኳን በአግባቡ አይመቻችልንም፡፡
 ተማሪዎቹን ማግኘት የምንችለዉ ከትምህርት ስዓት ዉጭ ማለትም ቅዳሜና እሁድ
እንዲሁም ከሰኞ እሰከ አርብ ከ 11፡00 በኋላ በመሆኑ ስራዉን በአግባቡ ለመስራት የትርፍ ስዓት
ክፍያና ትራንስፖርት አለመመቻቸት፣

በመሆኑም ዳይሬክቶሬቱ በ 2014 በጀት ዓመት የተከናወኑ ጠንካራ ተግባራትን በማጎልበት እና የነበሩትን ክፍተቶች እንደ
መነሻ በመያዝ በማድረግ የ 2015 በጀት ዓመት የሚሰሩት የስራ እቅድ በዝርዝር እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
3.የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከ.መቆ ዳይሬክቶሬት የ 2014 ዓ.ም ዋና ዋና
ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ

3.1. የተገልጋይ እርካታ ከማሳደግ አንጻር የተሰሩ ስራዎች የሁኔታ ግምገማ


-ለደንበኞች የሚሠጡ አገልግሎቶች ተገልጋዮችን ሚያረኩ ስለመሆኑ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ እና ግብረመልሶችን
በመመርመር ተገልጋዮችን የሚያረካ አገልግሎት መስጠት ችለናል፡፡

3.2.የሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ከማሻሻል አንጻር የተሰሩ


ስራዎችየሁኔታ ግምገማ
- የአላቂ ንብረቶችን በተቻለ መጠን ያለምንም ብክነት ለመጠቀም ያቀድነው እቅድ በሚገባ እና ለወደፊቱም አርአያ
በሚሆን መልኩ ማሳካት ችለናል እንዲሁም ንብረቶችን በካይዘን በማደራጀት ከብልሽትና ብክነት መከላከል ተችሏል፡፡

በተጨማሪም ስለ ፈንዱ ጥቅም ለማህበረሰቡ በማስረዳት የፈንድ አባላትን ከ 860 ላይ 108 አዳዲስ አባለትን
በመጨመር የፈንድ አባላትን ቁጥር ወደ 968 ማሳደግ ተችሏል ያቀድነውንም እቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ተችሏል
በሚቀጥለው የበጀት አመት ከዚህ የተሸለ ለመስራት ከሁሉም የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያወች ጋር ስምምነት ተደርሷል፡፡
- አላቂ ንብረቶችን በተቻለ መጠን ያለብክነት መጠቀም እና ንብረቶችን በካይዘን በማደራጀት ከብልሽትና ብክነት
መከላከል ተችሏል፡፡
-በተጨማሪም ስለ---- ፈንድ ጥቅም ለማህበረሰቡ በማስረዳት የፈንድ አባላትን ቁጥር መጨመር ተችሏል፡፡
በሚቀጥለው በጀት አመትም ከዚህ በተሻለ ለመስራት ከዳይሬክቶሬቱ ባለሙያወች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

3.3 .በ 2014 ዓ.ም ድጋፍና እንክብካቤ ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ስራዎች የሁኔታ ግምገማ
- ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉን የማህበረሰብ ክፍሎች እና በኤች.አይ.ቪ ምክንያት የተጎዱ ማህበረሰቦችን መደገፍና መንከባከብ
ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አንዱ መንገድ እንደመሆኑ መጠን በ 2014 በጀት ዓመት በኤች.አይ.ቪ
ምክንያት ለተጎዱ የአካባቢው ህጻናት በየወሩ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ የሚደረግላቸው ልጆችን አሁንም
ድጋፉን ማስቀጠል ተችሏል፣
-ከእድገት በስራ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በደማቸው ያለባቸው ሰራተኞች እና ተማሪዎች ማህበር ጋር
በመተባበር በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ 25 ህጻናትን በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ 5
ትምህርት ቤቶች በመመልመል ለእያንዳንዳቸው 10 ኪሎ ግራም መኮረኒ ድጋፍ ተደርጓል፣በተመሳሳይ
በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ለ 22 ህጻናት
ለእያንዳዳቸው 1000 ብር ወጭ በማድረግ የትምህርት ቁሳቁስ እና ዩኒፎርም ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡
- በተጨማሪም በሁሉም ግቢ ለሚገኙ እና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ 140 ሴት ተማሪዎች I CARE FOR THE
NATION ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በተገኘ ድጋፍ በየወሩ 100 ብር ለጸጉራቸው ማሰሪያ እንዲሁም
የ 110 ብር የኮፒ እና የፕሪንት አገልግሎት እናዲያገኙ ተመቻችቶላቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘም
በተጨማሪም የ I CARE FOR THE NATION መስራች የሚደገፉ ተማሪዎችን በአካል በማግኘት ስለ
በራስ መተማመን ስልጠና ተሰጥተዉ ል በዛው እለትም ለሁሉም ተማሪዎች ለእያንዳዳቸው 2 የውስጥ ሱሪ እና 2
የልብስ ሳሙና ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡ እነዚህን እና ሌሎች ተግባራትን ያከናዎን ቢሆንም በመጭዉ በጀት ዓመት ያልተሰሩ
ስራዎችን ነቅሰን በማዉጣት ሌሎች ሊሰሩ የሚገባቸዉን በመጨመር ታቅዶ መሰራት እንዳለበት በማመን የገመገምን ሲሆን
በአጠቃላይ ከድጋፍና እንከብካቤ አንጻር ከፍተኛ አፈጻጸም አስመዝግበናል፡፡

3.4. በ 2014 ዓ.ም ኤች አይቪን ከመቆጣጠር አንጻር የተሰሩ ተግባራት የሁኔታ ግምገማ
- ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ እና NAPPAD ከተባለ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት በድጋፍ ያገኘነውን
የወንድ ኮንዶም አሰራጭተን ስለ አቅርቦትና ስርጭት እና አጠቃቀሙ መረጃ ተስጥቷል፡፡

- ለ 17 የክሊኒክ ባለሙያዎች የኤች አይ.ቪ ምርመራ እና የምክር አገልግሎት ስልጠና ለአምስት ቀናት ተሰጥቷል፡፡
በዚህም አፈጻጸማችን የሚያበረታታ ነው በ 2014 ዓ.ም የነበሩ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር የታዩ ክፍተቶችን
በሚገባ በመረዳት ለ 2015 ዓ.ም ማቀድና መተግበር እንደሚገባ የተረዳንበት ዓመት ነበር፡፡ አጠቃላይ ኤች.አይ.ቪን
ከመቆጣጠር አኳያ የተተገበረዉ የዕቅድ አፈጻጸም ከፍተኛ እንደነበር ገምግመናል፡፡

3.5 . በ 2014 ዓ. ም ኤች.አይ.ቪን ከመከላከል አንጻር የተሰሩ ተግባራት የሁኔታ ግምገማ


- ኤች.አይ.ቪን ለመከላከል ዳይሬክቶሬቱ በዩኒቨርስቲዉ ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችና ከዩኒቨርስቲዉ ዉጭ ባሉ መንግስታዊ እና
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ የታቀዱ ስልጠናዎች፣የአቻ ለአቻ ዉይይቶች፣ የጸረ አደንዛዥ ዕጽ ግንዛቤ ማስጨበጫ
የውይይት መነሻ ሐሳብ በዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በማቅረብ ተጋላጭ ከሆኑ ተማሪዎች ጋር ወይይት ተደርጓል፣ ማህበረሰቡን
በስነ-ተዋልዶ ጤና እና ኤች.አይ.ቪ ዙሪያ አቅም የሚገነቡ በራሪ ፅሁፎች ተዘጋጅተዉ ቀርበዋል፡፡ የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም
ለዩኒቨርስቲው መምህራን እና የዳይሬክቶሬቱ ሰራተኞች የአቻ ለአቻ የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT)
የተሰጠ ሲሆን በዚህም አፈጻጸማችን የሚያበረታታ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች የታቀዱት ስልጠናዎች ሙሉ በሙሉ
አለመፈጸማቸዉ፣ በአቻ ለአቻ ዉይይት የሚጠበቀዉን ያክል ሰዉ አለመድረስ እንደ ክፍተት የተገመገመ ሲሆን በ 2014 ዓ.ም
የነበሩ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን በሚገባ በመረዳት ለ 2015 ዓ.ም ማቀድና መተግበር እንደሚገባ
የተረዳንበት ዓመት ነበር፡፡ አጠቃላይ ኤች.አይ.ቪን ከመከላከል አኳያ የተተገበረዉ የዕቅድ አፈጻጸም ከፍተኛ እንደነበር
ገምግመናል፡፡

3.6. በ 2014 ዓ.ም የለዉጥ መሳሪያዎችን ከማስፈጸም አኳያ የተሰሩ ስራዎች የሁኔታ
ግምገማ
- በበጀት ዓመቱ የልማት ሰራዊት ከመገንባት፣ እና ዕቅድን በቢ.ኤስ.ሲ ከማቀድና ከማከናወን፣ የካይዘን ፍልስፍና
ትግበራ፣ የስራ ስታንዳርድ አዉጥቶ ከመስራትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ነቅሶ ከማዉጣትና ከመተግበር አንጻር
ከፍተኛ ዉጤት ታይቷል፡፡ ሆኖም የለዉጥ መሳሪያዎችን በአግባቡ በመተግበር ለስራችን ዉጤት መሻሻል ከፍተኛ
አስተዋጽኦ እንደሚያመጣ በማመን ለ 2015 ዓ.ም በተሻለ ለመተግበር ታስቦ ሰፊ እቅድ ተይዟል፡፡

4. በዳይሮክቶሬቱ አገልግሎቱን የሚያገኙ ደንበኞች


 የባ/ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች

 የባ/ዳር ዩኒቨርስቲ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች


 የባ/ዳር ከተማ እና አካባቢዉ ማህበረሰብ

5. የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና አጋር አካላት


 ፕሬዚደንት ጽ/ቤት እና ሌሎች የዩኒቨርስቲዉ የስራ ክፍሎች

 አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት

 ማህበረሰብና ምርምር አገልግሎት ተቀዳሚ ዳይሬክቶሬት

 ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምርት ሚኒስቴር

 የአማራ ክልል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ

 የባ/ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት

 የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ባ/ዳር ቅርንጫፍ

 የኢትዮጵያ ምግብ መድሀኒት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን ባህር ዳር ቅርንጫፍ


ሠንጠረዥ 1.ባለድርሻ አካላት

ተ.ቁ የባለድርሻ አካላት ስም የባለድርሻ አካላት ፍላጎት ዳይሬክቶሬቱ ከባለ ድርሻ አካላት የሚፈልገዉ ባህሪያት የባለድርሻ አካላት ፍላጎት ባይሳካ የተጽእኖ
ዳይሬክቶሬቱ ላይ ሊደርስ የሚችለዉ ደረጃ
ጉዳት

1 ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በጀት መፍቀድና በበላይንት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በመታባበርና በጋራ መስራት ስለማይቻል እቅድን ከፍተኛ
መቆጣጠር በጋራ መስራት መፈጸም አይቻልም

2 አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ከዳይሬክቶሬቱ ጋር በመሆን የዩኒቨርስቲዉን ግብ ያማከለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ተማሪዎች ኤች.አይ.ቪ /ኤድስን ከፍተኛ
ስልጠናወችን በጋራ መስጠት ለመቆጣጠር የመታባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ የመከላከል ባህሪያቸዉ ይቀንሳል

3 ምርምርና ማህበረሰብ በአደንዛዥ እጽ እና በአሉታዊ መጤ የዩኒቨርሲቲዉን ግብ ያማከለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና በአደንዛዥ እጽ እና በአሉታዊ መጤ ከፍተኛ
አገልግሎት ተቀዳሚ ልማዶች ዙሪያ አብሮ መስራት ለመቆጣጠር የመታባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ ልማዶች ዙሪያ የተማሪዎች ግንዛቤ
ዳይሬክቶሬት ይቀንሳል

4 የፌደራል ኤች.አይ ቪ/ኤድስ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት የዩኒቨርስቲዉን ግብ ያማከለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና አዳዲስ መረጀዎችን የማግኘት ክፍተት መካከለኛ
መከላከልና መቆጣጠር ጽ/ቤት ለመቆጣጠር የመተባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ ይኖራል

5 የአማራ ክልል ኤችአይ ቁሳዊ እና ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ የዩኒቨርሲቲዉን ግብ ያማከለ ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላከልና ተማሪዎች የተሟላ አገልግሎት አያገኙም መካከለኛ
ቪ/ኤድስ መከ/መቆ ቢሮ ለመቆጣጠር የመተባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ

6 የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሙያዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ መስጠት ዩኒቨርስቲዉን ግብ ያማከለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ተማሪዎች የተሟላ አገልግሎት አያገኙም ከፍተኛ
ጤና መምያ ኤች.አይ.ቪ /ኤድስ ለመቆጣጠር የመታባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ
መከ/መቆ ጽ/ቤት
7 የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ በስነ-ተዋልዶ ዙሪያ ሙያዊ እና ዩኒቨርስቲዉን ግብ ያማከለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና በስነ-ተዋልዶ ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ከፍተኛ
ባህርዳር ቅርንጫፍ ቁሳዊ ድጋፍ መስጠት ለመቆጣጠር የመታባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ ይቀንሳል

8 የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት አደንዛዥ እፅ የሚጠቀሙ ዩኒቨርስቲዉን ግብ ያማከለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ የሆኑ ከፍተኛ
አስተዳደር ና ቁጥጥር በመጀመር ዉስጥ ያሉ ተማሪዎች ለመቆጣጠር የመታባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ ተማሪዎችም ሆነ በመጀመር ዉስጥ ያሉ
ባለስልጣን ባህር ዳር ቅርንጫፍ ስልጠና ሲወስዱም ሆነ ለማወያየት ተማሪዎችን ከሱስ ማዉጣትም ሆነ
ተማሪዎችን ምቹ ሁኔታዎችን እንዳይገቡ ለመከላከል አስቸጋሪ ይሆናል
በመፍጠር እገዛ ያደርጋሉ

ሰንጠረዥ 1.የተገልጋይ አካላት ፍላጎት ትንተና

የትኩረት መስክ ተገልጋይ/ደንበኞች ከዘርፉ የሚፈልጉት አገልግሎት የሚፈልጉት ባይፈጸም የሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽእኖ የተጽዕኖ
ደረጃ

ኤች.አይ.ቪ ኤድስን አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ስልጠና መስጠት ኤች.አይ.ቪን የመከላከሉን ስራ ውጤት ይቀንሳል ከፍተኛ
መከላከል

ተማሪዎች፣መምህ የቡና ጠጡ ቶክ ሸዉ የሚኒ ሚዲያ እና የስነ-ፅሁፍ ፕሮግራሞችን ማመቻቸት ኤች.አይ.ቪን የመከላከሉን ግንዛቤ ይቀንሳል ከፍተኛ
ራን እና ለተማሪዎች፣መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች
የአስተዳደር
ሰራተኞች የተዋልዶ ጤና የሜንተር ሽፕ ስልጠና መስጠት ለተማሪዎች በስነ-ተዋልዶ ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ይቀንሳል ከፍተኛ

ለተማሪዎችና ሰራተኞች የእህቶች ለእህቶች የአማቻቾች ስልጠናና ዉይይቶችን ለሴት ኤች.አይ.ቪን የመከላከሉን ስራ ውጤት ይቀንሳል ከፍተኛ
ተማሪዎች፣መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች

የአቻ ለአቻ የተማሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ኤች.አይ.ቪን የመከላከሉን ግንዛቤ ይቀንሳል ከፍተኛ

አካል ጉዳተኛ ለሆኑ የዩኒቨርስቲዉ ተማሪዎች ምቹ የሆኑ የባህሪ ለውጥ ተግባቦት የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ላይ ኤች.አይ.ቪን
ማስተማሪያ መንገዶችን (ለምሳሌ የምልክት ቋንቋ፤የብሬል ጽሁፍ እና ሌሎች የመከላከሉን ስራ ውጤት ይቀንሳል፣ተጋላጭነታቸውንም
ከፍተኛ
ስልቶችን) በመጠቀም ግንዛቤያቸውን ማሳደግ ማሰልጠን ተማሪዎች፣መምህራን እና ይጨምራል
የአስተዳደር ሰራተኞች

ተማሪዎች፣መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የኤች.አይ.ቪን መከላከል የግንዛቤ እጥረት ያጋጥማል


መልክቶትና ትምህርት አዘል (SBCC) ማቴሪያሎችን ማሰራጨት
ከፍተኛ

መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የስራ ቦታ የማህበረሰብ ዉይይት ማካሄድ የኤች.አይ.ቪን የመከላከሉን ግንዛቤ ይቀንሳል ከፍተኛ

ለተማሪዎች፣መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የሚኒ ሚዲያ እና የስነ-ፅሁፍ የኤች.አይ.ቪን የመከላከሉን ግንዛቤ ይቀንሳል ከፍተኛ
ፕሮግራሞችን ማመቻቸት
ኤች.አይ.ቪ /ኤድስን ተማሪዎች፣መምህ ለተማሪዎች፣መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የኮንዶም ስርጭት ማካሄድ የኤች.አይ.ቪን እና ተያያዥ የአባላዘር በሽታ እንዲሁም ያልተፈለገ በጣም
መቆጣጠር ራን እና እርግዝና ይስፋፋል ከፍተኛ
የአስተዳደር
ለተማሪዎች የአባላዘር በሽታ ምርመራና ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ማመቻቸት በበሽታው ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ በጣም
ሰራተኞች
አለመከታተል፣ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው መቅረት ከፍተኛ

ለተማሪዎች፣ለሰራተኞች የኤች.አይ.ቪ ምርመራ እንዲሰጥ ማመቻቸት የኤች.አይ.ቪ ስርጭት እዲጨምር ምክንያት ይሆናል በጣም
ከፍተኛ

ተማሪዎች ምቹ የሆነ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት እንዲኖር ማመቻቸት ተማሪዎች ላልተፈለገ እርግዝና እና የስነ-ተዋልዶ ችግር ተጋላጭ በጣም
ይሆናሉ ከፍተኛ

መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ትኩረት ያደረገ የኮንዶም ስርጭትን ማካሄድ የኤች.አይ.ቪን እና ተያያዥ የአባላዘር በሽታ እንዲሁም ያልተፈለገ ከፍተኛ
እርግዝና ይስፋፋል

ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ላለባቸዉ የዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ ኢኮኖሚ፣ የስነልቦናና ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸው የዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ በጣም
ድጋፍና እንክብካቤ የህግ ድጋፍ ማድረግ በስነ ልቦና ይጎዳሉ ከፍተኛ
ተማሪዎች፣መምህ
ማድረግ
ራን እና ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ላለባቸዉ የዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ ስለ ጸረ-ኤድስ ህክምናና በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት ከትምህርት እና ስራ ገበታ በጣም
የአስተዳደር እና ተጓዳኝ በሽታዎች ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ የሚቀሩ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ቁጥር መጨመር ፣ ከፍተኛ
ሰራተኞች በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት የሚከሰት የሞት መጠን መጨመር

በኤች.አይ.ቪ ምክንያት ለተጎዱ ህጻናትና ወጣቶች የስነልቦና፣ የማህበራዊ፣ የህግና ከኤች.አይ.ቪ ነጻ ትውልድ የማፍራት ዕቅዱ ውጤታማ እዳይሆን ከፍተኛ
የኢኮኖሚ ድጋፍ እንዲያገኙ ማመቻቸት ያደርጋል
ተቋማዊ ለዉጥ የካይዘን ትግበራን ማሳደግ፣የውጤት ተኮር ዕቅድን ተግባራዊ ማድረግ የተገልጋዮች እርካታ መቀነስ ከፍተኛ
መሳሪያዎችን ተግባር ላይ
ማዋል
6. የሁኔታ ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመቆጣጠርም ሆነ ለመከላከል ያስመዘገብናቸዉ ዉጤቶች ጥሩ ቢሆኑም በወቅታዊ
ሁኔታወችና ለክፍሉ ያለዉ የማህበረሰቡ አመለካከት ዝቅተኛ በመሆኑ ማስመዝገብ ያለብንን ዉጤት አላስመዘገብንም
ስለሆነም ከላይ የተዘረዘሩትን ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማሰቀጠል እንዲሁም ክፍተቶቻችንን በማሻሻልና በመድፈን
በስነ-ተዋልዶ እና ተያያዥ ችግሮች ላይ በተሻለ መልኩ ከዉስጥም ሆነ ከዉጭ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት
(stakeholder) ጋር ቅንጅት በመፍጠር የተማሪዎች ጤንነት ተጠብቆ የዩኒቨርስቲዉን ግብና ራዕይ ለማሳካት ብሎም
የሀገሪቱን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ስርጭት መቀነስ በ 2021-2025 ያቀደችዉን ግብ ለማሳካት የበኩላችንን አስተዋፆ
ለማበርከት ለ 2015 የበጀት ዓ.ም ትልቅ ትኩረት በመስጠት እንደሚከተለው አቅደናል፡፡

7. የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች እና መሪ ቃል

7.1.ተልዕኮ
አገሪቱ የምትፈልገውን በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል በብዛትና በጥራት በማፍራት፣ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው
ጥናትና ምርምሮች በማድረግና የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ለአገራዊ ብሎም ዓለማቀፋዊ ዕድገት ጉልህ
አስተዋጾኦ ማድረግ፡፡

7.2.ራዕይ
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 2030 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቀዳሚው፤በአፍሪካ ከሚገኙ ግንባር ቀደም የምርምር
ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆን፡፡

7.3.እሴቶች
በቅርቡ በጸደቀዉ የሰኔት ህግ መሠረት በመዘጋጀት ላይ ባለዉ ስልታዊ እቅድ መሠረት እሴቶቻችን
 ጥበብን ፍለጋ (Pursuit of Wisdom)
 ልህቀት (Excellence)
 ፈጠራ (Innovation)
 ማህበራዊ ኃላፊነት ( Social responsibility)
 ብዝኃነት (Diversity)
 ዓለም አቀፋዊነት (Internationalization)

7.4.መሪ ቃል
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ (Wisdom at the source of the Blue Nile)

8. የ 2015 በጀት ዓመት እቅድ መነሻዎች


 የዩኒቨርስቲው ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች እና መሪ ቃል፣
 ከ 2021-2025 የብሄራዊ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እስትራቴጅ

 አለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል እቅድ

 የተለያዩ ጥናቶች

 ከደንበኞች የተገኘዉ ግብረ መልስ

 የ 2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ናቸው፡፡

9.የዳይሬክቶሬቱ የትኩረት መስኮች


 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን መከለከል

 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን መቆጣጠር

 ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ

 ተቋማዊ ለዉጥ መሳሪያዎችን ተግባር ላይ ማዋል

10. የ 2015 ዓ.ም ግብዓት ማሟላትና ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አፈፃጸም

10.1. ከአመለካከት ግንባታ አንፃር የተሰሩ ስራዎች


 በ 2014 ዓ.ም የነበሩብንን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ከየግቢው ባለሙያወች ጋር በአንድነት

ግምገማ በማድረግ በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር እና ደካማ ጎኖችን በማሻሻል ወደ


ስራ መሰማራት ተችሏል፣
 ከ 2014 የእቅድ ክንውን ግምገማ በመነሳት በ 2015 በጀት ዓመት ላይ መከናወን የሚገባቸውን

የትኩረት መሰኮች በመለየት እንዲሳኩ የሚረዱ ዝግጅቶችን አካሂደናል፡፡

10.2. ግብዓት ማሟላት


 ተማሪዎችን ከ ስለኮረና እና ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ እንዲሁም ስለስነ-ተዋልዶ ግንዛቤ የሚያሳድጉ እና

ችግሮችን ለመከላከል የሚረዱ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን እንዲዘጋጁ መግባባት ላይ


ተደርሷል፣፡፡
 ተማሪዎች ወደ ግቢ እንደገቡ የመጀመሪያ ቀን የመረጃ ማእከላችን ክፍት እንዲሆን ቅድመ

ዝግጅት ተደርጔል፣
 የኮንድዶም አቅርቦትን በሚመለከት እስካሁን ድረስ ድጋፍ ሲያደርጉልን የነበሩ ተቋማት በሀገር
አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮንዶም እጥረት ምክንያት ሲያደርጉልን የነበረውን ድጋፍ
ስላቋለረጡብን የዝግጅት ምዕራፋችን የተሟላ እንዳይሆን እንቅፋት ፈጥሮብናል፡፡

11.የዩኒቨርስቲዉ የአስር ዓመት ስትራቴጂካዊ እቅድ ለማሳካት በዳይሬክቶሬቱ የተወሰዱ ግቦች


ዩኒቨርሲቲው በ 2013 ዓ.ም በአዘጋጀው የ 10 ዓመት ስትራቴጂክዊ ዕቅድ (2020/21-2029/30) 11 ግቦች
ተቀምጠዋል፡፡ ከእነዚህ ግቦች ውስጥ ከኛ ዳይሬክቶሬት ተልዕኮ ጋር የተቀራረበውን ወይም የሚመለከተንን ግብ
እንደሚመለከተዉ ወስደናል፡፡

ግብ 1.የትምህርት ጥራት፤አግባብነት እና ተደራሽትን ማረጋገጥ

ግብ 6.የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ

ግብ 7.ተቋማዊ አመራርን፣ አመለካከትን፣ አደረጃጀትንና አሰራሮችን ማሻሻል

ግብ 8. የሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ማሻሻል

ግብ 9.ዘርፈብዙ ተግባራትን አካቶ (Mainstreaming) መስራት የሚያስችል አደረጃጀትና

አሰራር መፍጠርና ማጠናከር

12.የዳይሬክቶሬቱ የ 2015 በጀት አዓመት ግቦች


የዳሬክቶሬቱ ዋና አላማ ሀገሪቱ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ 2021-2025 ባወጣችዉ ስተራቴጅ
እቅድ ያስቀመጠችውን ግብ ከዩኒቨርሲቲዉ ከወሰድናቸዉ ግቦች ጋር በማቀናጀትና ተመሳሳዩን በመዉስድ በመተግበርና
የዩኒቨርሲቲዉን ራዕይ በመሳካት የበኩላችንን አስተዋጾ ለማድረግ ዳሬክቶሬቱ የራሱን ግቦች ቀርጿል፡፡

ግብ 6.1 የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ

ግብ 6.2 የሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ማሳደግ

ግብ-3፡ የድጋፍ እንክብካቤ አገልግሎትን ማሻሻል

ግብ 6.4 ኤችአይቪ/ኤድስን ለመቆጣጠር የኤች አይቪ/ኤድስን አገልግሎቶችን (Biomedical


intervention) ማስፋፋት

ግብ 6.5 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስንለመከለከል.ኤች.አይ.ቪን ና በተያያዥ ችግሮች ዙሪያ ያለዉን ግንዛቤ


ማሳደግ (Beheveral intervention)

ግብ 6.6 ተቋማዊ አመራርን፣ አመለካከትን፣ አደረጃጀትንና አሰራሮችን ማሻሻል


ግብ 6.7 ዘርፈብዙ ተግባራትን አካቶ (Mainstreaming) መስራት የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር
መፍጠርና ማጠናከር

13. የግቦች የአፈጻፀም አቅጣጫ


ለአፈጻጸም ይመቸን ዘንድ በአራቱ እይታዎች ማለትም በተገልጋይ፣በፋይናንስ፣በውስጥ አሰራር እና መማርና ዕድገት
በየራሳቸው ስር ግቦችን እስከ ማስፈጸሚያ ስልታቸዉ በመተንተን እነደሚከተዉ አስቀምጠናል፡፡

ግብ 6.1 የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ

ዳይሬክቶሬቱ የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች በማበራከትና በማሻሻል ለደንበኞቻችን ቀልጣፋና አግባብ ያለዉ መረጃና
የምክር አገልግሎት በመስጠት ለደንበኞች የሚሰጡ አገልግሎት ተገልጋዮችን የሚያረካ ስለመሆኑ ክትትልና ድጋፍ
ማድረግ ግብረመልስ በማዘጋጀትና የተገልጋዮችን እርካታ በመለካት ዳይሬክቶሬቱ ለዩኒቨርሲቲዉ ራዕይ መሳካት
የድርሻዉን ያበረክታል የሚሰራቸውም ስራዎች የሚከተሉት ናቸው

 የአገልግሎት ስታንዳርድ ማውጣት


 ለደንበኞች የሚሰጡ አገልግሎት ተገልጋዮችን የሚረካ ስለመሆኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
ብ 6.2.ሀብት
ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት በማሻሻል ለሚደገፉ ወገኖች
ድጋፍን ማሳደግ
ዳይሬክቶሬቱ ለቢሮ አገልግሎት የተረከባቸዉን ቋሚና አላቂ ንብረቶችን ከብለሹ አሰራር በፀዳ መልኩ በመጠቀም እና
ከአጋር ድርጅቶች ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ሀብት በማመንጨት እና የተለያዩ ስልጠናዎችን በማሰጠት ድጋፍ ለሚሹ
ወገኖች ድጋፍ ማሰባሰብ ከተለያዩ መንግስታዊ ከሆኑና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየሰራቸዉ ያሉትን ተግባራት
በይበልጥ በማጠናከር እዉቀትን ሀብትን በማቀናጀት እና በጋራ በመስራት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን እና ተዛማጅ የስነ-ተዋልዶ
ጤና ችግሮችን የመቆጣጠር ስራዎችን መተግበር

 የተለያዩ ፕሮፖዛሎችን በመንደፍ የገንዘብና የሙያ እገዛ ማግኘት

 ንብረቶችን በካይዘን በማደራጀት ከብልሽትና ብክነት መከላከል

 በክፍሉ ያሉትን ንብረቶች በአግባቡ ተመዝግበዉ እንዲያዙ ና ለተገቢዉ አገልግሎት መጠቀም

 ስለ ፈንዱ ጥቅም ለማህበረሰቡ በማስረዳት የፈንድ አባላትን ማበራከት


ግብ 6.3 የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎትን ማሻሻል
ዳይሬክቶሬቱ በመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች የበጎ ፈቃደኝነት ጽንሰ ሀሳብን በማስረጽ እና ሀብት በማሰባሰብ
ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እገዛ በማድረግ ድጋፍ ለሚሹትም ድጋፍ በማድረግ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን
እና ተዛማጅ የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮችን የመቆጣጠር ስራዎችን መተግበር፡፡ በመሆኑም የዩኒቨርስቲዉን ግብ 8 የተሳካ
እንዲሆን ዳይሬክቶሬቱ የሚመለከተዉን ዝርዝር ተጋባራት አስቀምጧል፡፡

 ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ላለባቸዉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰራተኞችና ተማሪዎች የስነልቦና፣ የማህበራዊ፣ የህግና
የኢኮኖሚ ድጋፍ እንዲያገኙ ማመቻቸት

 በኤች.አይ .ቪ ምክንያት ለተጎዱ የአካባቢው ህጻናት በየወሩ ድጋፍ ማድረግ

 ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ላለባቸዉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰራተኞች እና ተማሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ
ስልጠና መስጠት

 ለኤድስ ፈንድ ኮሚቴ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ


ግብ 6.4.ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመቆጣጠር የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን አገልግሎቶችን
(Biomedical intervention) ማስፋፋት
ዳይሬክቶሬቱ ከተለያዩ መንግስታዊ ከሆኑና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየሰራቸዉ ያሉትን ተግባራት በይበልጥ
በማጠናከር እዉቀትን ሀብትን በማቀናጀት እና በጋራ በመስራት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን እና ተዛማጅ የስነ-ተዋልዶ ጤና
ችግሮችን የመቆጣጠር ስራዎችን መተግበር በመሆኑም ከዚህ የሚከተለዉ ዝርዝር ተግባራት እንደሚከተለው
ተቀምጠዋል፡፡

 የኤች.አይ.ቪ ምርመራ እንዲሰጥ ማመቻቸት

 ለክሊኒክ ሰራተኞች የአባላዘር በሽታዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ማሰጠት

 ለወጣቶች ምቹ የሆነ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት እንዲኖር ማመቻቸት

 ለተቋሙ ሠራተኞችን ትኩረት ያደረገ የኮንዶም ስርጭትን ማካሄድ

 ለተማሪዎችን ትኩረት ያደረገ የኮንዶም ስርጭት ማካሄድ


ግብ 6.5 ዘርፈብዙ ተግባራትን አካቶ (Mainstreaming) መስራት የሚያስችል
አደረጃጀትና አሰራር መፍጠርና ማጠናከር
በየኮሌጆች/ፋኩሊቲዎች/ ስኩል ኦፍ ኢኒስቲቲዩት ላሉ ዲኖች/የትምህርት ክፍሎች/ማኔጅንግ ዳይሬክተሮች እና
ለአካባቢዉ ማሀበረስብኤች ስልጠና በመስጠትና እና የአቅም ግንባታ ስራዎቸን በመተግበር እንዲሁም ስለ
ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ትክክለኛ ወቅታዊ መረጃ በመሰጠት የተዋልዶ ጤና እና ተዛማጅ ጉዳዮችን አካተዉ
(Mainstreaming) እነዲሰሩ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በ 2020 በአለም አቀፍ የተነደፈዉን እና ሀገሪቱ
የተቀበለችዉን እቅድ ማሳካት እንደዚሁም ከአደንዛዥ-እጽ ተጠቃሚነት እና ከተዋልዶ ጤና ችግሮች የጸዳ ጤነኛ
ትዉልድ እንዲፈጠር ና የዩኒቨርስቲዉ ራዕይ እንዲሳካ ዳይሬክቶሬቱ የድርሻዉን ይወጣ ዘንድ ዝርዝር ተግባራት
እንደሚመለካተዉ ተቀምጠዋል፡፡ ፡፡

 ሥልጠና መስጠትና ሁሉም የዩኒቨርስቲዉ ክፍሎች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን የመከላከል ተግባራትን አካትተዉ


እንዲተገብሩ ማስተባበር ክትትል ማድረግ
ግብ 6.6 ተቋማዊ አመራርን፣ አመለካከትን፣ አደረጃጀትንና አሰራሮችን ማሻሻል
በዳይሬክቶሬቱ ሥር ያሉትን የተለያዩ አደረጃጀቶች በመጠቀም የካይዘን ትግበራን ማሳደግ፣የመልካም አስተዳደርን ፅንሰ
ሀሳብ ማስረፅ እና የዉጤት ተኮር እቅድን ተግባራዊ በማድረግ አሰራሮችን በማሻሻል ለግቡ መሳካት አስተዋፆ ለማድረግ
ዝርዝር ተግባራት እንደሚመለካተዉ ተቀምጠዋል፡፡፡፡

 በዉጤት ተኮር ዕቅድ ላይ የተመረኮዘ የስራ ሥርዓት እንዲሰፍን መደገፍ መከታተል

 በዳይሬክቶሬቱ ስር ያሉ የጸረ የኤች.አይ.ቪ ክበባትና ማህበራትን ድጋፍና ክትትል ማድረግ

 የ 2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድና የተሸሉ ተሞክሮችን ለሌሎች ማካፈል

 የጸረ ሱስ ክበባትን መደገፍ እና ክትትል ማድረግ

 የመረጃ ማእከላትን ማጠናከር


 ከአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የጸረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ፎረም ጋር ያለውን አጋርነት በማጠናከር መሳተፍ
ግብ 6.6 ተቋማዊ አመራርን፣ አመለካከትን፣ አደረጃጀትንና አሰራሮችን ማሻሻል

ግብ 6.7 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከለከል ኤች.አይ.ቪን እና በተያያዥ ችግሮች ዙሪያ


ያለዉን ግንዛቤ ማሳደግ (Beheveral intervention)
የክፍሉን ሰራተኞች በስነ-ተዋልዶ ና ተያያዥ ችግሮች ዙሪያ የተለያዩ አጫጭር ስልጠናወችን በማዘጋጀትና ያሉብንን
የእዉቀት እና ክህሎት ክፍተቶች በመሸፈን እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ልምድ ልዉዉጥ በማድረግ የተሸሉ
ተሞክሮችን በማምጣት የክፍሉን ሰራተኞች አቅማቸዉን ማጎልበት፡፡በስራ ግምገማ ያየናቸዉን ክፍተቶችን በመሸፈንና
ግንዛቤ በመፍጠር ለተማሪዎች በሚሰጡ አግልግሎቶች ሙሉ እንዲሆኑ ማድረግና እንዲሁም የተዋልዶ ጤና ችግሮችን
ለመከለከል የሚያስችል የህይወት ክህሎትን በተማሪዎች ላይ በማሳደግ ጊዜያቸዉን በሚገባ ለትምርታቸዉ በመጠቀም
የተማሪዎችን የማቋረጥ መጠን መቀነስና የመመረቅ ምጣኔን ማሳደግ ይቻላል፡፡ በመሆኑም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከ/መቆ
ዳይሬክቶሬት የትምህርትን ጥራት አግባብነት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ለዩኒቨርስቲዉ ራዕይ መሳካት ጉልህ
አስተዋጽኦ ለማድረግ ለዚህ ግብ ማስፈጸሚያ አቅጣጫ እንደሚመለከተዉ አስቀምጠናል ፡፡

 ለዩኒቨርስቲዉና የአካባቢዉ ማህበረሰብ አደንዘዥ እጽ ዙርያ ግንዛቤ መፍጠር

 ለአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ስልጠና መስጠት

 የኤች.አይ.ቪን መከላከል መልክቶች የያዙ መረጃና ስርፀት ትምህርት (SBCC) ማቴሪያሎችን ማሰራጨት

 የቡና ጠጡ ቶክ ሸዉ የሚኒ ሚዲያ እና የስነጹሁፍ ፕሮግራሞችን ማመቻቸት

 የተለያዩ ኩነቶችን ማክበር(የአለም ኤድስ ቀን፣ የጸረ-ሱስ ቀን…)

 የተዋልዶ ጤና የሜንተር ሽፕ ስልጠና መስጠት

 ለተማሪዎችና ሰራተኞች የእህቶች ለእህቶች የአማቻቾች ስልጠናና ዉይይቶችን ማካሄድ

 የአቻ ለአቻ የተማሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት

 የአቻ ለአቻ የተማሪዎች ዉይይት ማድረግ

 በዩኒቨርስቲዎች ሚኒ ሜዲያ/የማህበረሰብ ሬዲዮ በመደበኛነት በመጠቀም በሚኒ ሚዲያ ዕቅድ መሰረት


የኤችአይቪ መከላከል ትምህርቶች/መልዕክቶች እንዲያስተላልፉ መከታተልና ማጠናከር

 በኤች.አይ.ቪ ዙሪያ ለአካል ጉዳተኞች ግንዛቤ መስጠት

 የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ዩኒቨርስቲዎች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ

14. ከላይ የተጠቀሱት ስራዎች በመሰራታቸው የሚጠበቁ ውጤቶች


ጥራት ያላቸው የተለያዩ ስልጠናዎች ለግቢው ማህበረሰብ እንዲዳረስ ይደረጋል፤ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና ከስነ-ተዋልዶ
ችግሮች የጸዳ ትውልድ በመፍጠር የትምህርት ተደራሽነቱም ይሻሻላል፡፡ ስለሆነም የዩኒቨርስቲውን ማህበረሰብ ከጤና
እና ከተለያዩ የሱስ ችግሮች የመጋለጥ መጠን ይቀንሳል፡፡ በተለይም የሴት ተማሪዎች የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮችንና
በጤና ምክንያት የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ቁጥር ይቀንሳል፡፡ በአጠቃላይ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አግባብ ያለው
ስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ እውቀት እና ክህሎት በመስጠት በዩኒቨርስቲው ውስጥ ጤናማ እና ከተለያየ ሱሶች የፀዳ
ሃገር ተረካቢ ዜጋ ማፍራት የሚጠበቁ ውጤቶች ናቸው፡፡

15. ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች


ዳይሬክቶሬቱ ዕቅዱን ለመተግበር ሲንቀሳቀስ ሊገጥሙት የሚችሉ ችግሮችን በተቻለ መጠን መለየትና የመፍትሄ
አቅጣጫ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ዳይሬክቶሬቱ የ 2015 ዓ.ም ዕቅዱን ለመተግበር ሲንቀሳቀስ ሊያጋጥሙት
ይችላሉ ተብለው የተለዩ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 እቅዱን ለመፈጸም ትግበራ ሲጀምር የዩኒቨርስቲዉና የአካባቢዉ ማህበረሰብ በችግሩ ላይ ያለዉ አመለካከት
ዝቅተኛ መሆን (ኤች.አይ.ቪ ጠፍቷል ለምን ትደክማላችሁ) እንዲሁም ከፕሮግራሙ ጋር ተያይዞ የጥቅማ
ጥቅም ጥያቄ እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡

 ዕቅዱን ለመፈጸም የሚያስፈልጉ ግብአቶች በጥራት፣ በመጠንና በተፈለገው ጊዜ ያለማግኘት (ለምሳሌ የተለያዩ
ስልጠናዎች ሲዘጋጅ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፣ ኪት፣ የአባላዘር በሽታዎች መመርመሪያ መድሃኒት የመሳሰሉት)
ችግሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡

 ዕቅዱን ለመፈጸም የሚያስፈልግ ገንዘብ ያለማግኘት ችግሮች ሊያጋጥም ይችላል

 የሐገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ተማሪዎችን ለመሰብሰብ አዳጋች ሊሆን ይችላል

 በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮንደም እጥረት ምክንያት ለተማሪዎችም ሆነ ለዩኒቨርስቲው


ሰራተኞች ትኩር አድርገን የምናሰራጨው የወንድ ኮንደም ላይኖር ይችላል፡፡

16.የመፍትሄ አቅጣጫዎች
 ተማሪዎችን ሰብስቦ ስልጠና ከመስጠት ይልቅ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ
ለምሳሌ በራሪ ወረቀቶችን ፤ቪድዮ፤ብዙኃን መገናኛዎችን ወ.ዘ.ተ በመጠቀም ሀሳብን ማስተላለፍ

 ማህበረሰቡ በችግሩ ላይ ያለዉን ዝቅተኛ አመለካከት በቀላሉ ለመፍታት ለክፍል ሐላፊዎች በየግል የችግሩን
አሳሳቢነት እንዲገነዘቡት ማደረግ ከዚህም ባሻገር ሁሉም ማህበረሰብ በኤች.አይ.ቪ እና ተዛማጅ ጉዳዮች
ዉይይት እንዲያደርጉ ጥረት ማድረግ እንዲሁም የበጎ ፈቃደኝነትን ጽንሰ ሃሳብ እንዲሰርጽ ክትትል ማድረግ፡፡

 የቁሳቁስ እጥረት ችግርን ለመፍታት ከግቢው አመራር ጋር በቅርብ በመስራት የተለያዩ የግዥ ዘዴዎችን
ማሳለጥ፣ ከአጋር ድርጅቶች የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ ምናገኝበትን መንገድ መፈለግ አይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡

 የበጀት እጥረቶችን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጋር በቅርበት በመስራትና የተለያዩ አጋዥ ድርጅቶችን ስፖንሰር
በማፈላለግ እጥረቱን መቅረፍ/መፍታት እንደ አይነተኛ መሳሪያ የምንጠቀመው ይሆናል፡፡
17.የግንኙነት አግባብ
የእቅዱን አፈፃጸም በየሶስት ወሩ በመከታተል የሚገመገምበት አግባብ ሲሆን የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያወች እቅዳቸውን
ከማሳካት አንጻር ወርሃዊ የስራ አፈፃጸም ግምገማ ያካሂዳሉ፡፡

18. ማጠቃለያ
የዩኒቨርስቲያችን ራዕይ እዉን ማድረግ የሚቻለዉ ጤነኛ፣ በስነ-ምግባር የታነጹ እና በራሳቸዉ የሚተማመኑ ተማሪዎች
እና ሰራተኞችን በመፍጠር በመሆኑ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ/መቆ ዳይሬክቶሬትም ይህንን ራዕይ ከግብ ለማድረስ
ከፍተኛ ሃላፊነት ካለባቸዉ ክፍሎች አንዱ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን መስራት ከዳይሮክቶሬቱ የሚጠበቅ ቢሆንም
የኤች.አይ.ቪ እና ስነ-ተዋልዶ ጤና ጉዳይ በአንድ ክፍል ብቻ የሚተገበሩ ጉዳዮች ባለመሆናቸዉ የሁሉንም የዩኒቨርስቲዉ
ክፍሎች ተግባር እና እርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት
በጋራ እንድንሰራ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
ዝርዝር ተግባራት

የእይ የተ የተቋሙ ግብ የዳ የዳይሬክ ተሩ ግብ ዋና ዋና ክብደት መለኪያ የመለኪያ መነሻ ዒላማ ዓመታዊ መርሓ ግብር የሚወርድለት ስትራ
ታ ግ ተግባራ ክብደት/ቀመር ባለሙያ ቴ
ክብደ ት ኛ ኛ ኛ ኛ ጂ
ት ሩ ሩ ሩ ሩ ያ






እይታዎች


20 የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ የአገልግሎት ስታንዳርድ ማውጣት 10 በቁጥር በተዘጋጀ ስታንዳርድ ብዛት 1 1 1 - - - ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች እና
ለዳይሬክቶሬቱ
1 1 1 1 1 1
10
ለደንበኞች የሚሠጡ 10 በመቶኛ በደንበኞች የሚሠጡ ግብረ 95 95% 95 95% 95 95% 95 95% 95 95% 95 95% ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች እና
አገልግሎቶችተገልጋዮችንሚያ መልሶች ለዳይሬክቶሬቱ
ረካስለመሆኑ ድጋፍ
10
እና ክትትል ማድረግ
ደንበኞች

2
0
15 የሀብት ማመንጨት አስተዳደርና ቁጥጥር
የሀብት ማመንጨትየአላቂ ንብረት ያለምንም በመቶኛ ያለምንም 10 100% 10 100% 10100% 10 100%10 100%10 100%
ብክነት ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
ሥርዓት ማሻሻል አስተዳደርና ቁጥጥር ብክነት መጠቀም 2 የመጠቀም ምጣኔ እና ለዳይሬክቶሬቱ
ሥርዓት ማሻሻል ንብረቶችን በካይዘን 10
በመቶኛ ያልተበላሸ ቋሚ ንብረት 10 10 10 10 10 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
በማደራጀት ከብልሽትና በመቶኛ 100% 100% 100% 100% 100% 100% እና ለዳይሬክቶሬቱ
2
ብክነት መከላከል
የተለያዩ ፕሮፖዛሎችን በቁጥር በተዘጋጀ ፕሮፖዛል ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
በመንደፍ የገንዘብና 2 ብዛት 3 4 1 1 2 እና ለዳይሬክቶሬቱ
የሙያ እገዛ ማግኘት
ስለ ፈንዱ ጥቅም በቁጥር 55 45 47 51 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
ለማህበረሰቡ 2 በፈንዱ አባላት 860 1024 901 942 983 1024 እና ለዳይሬክቶሬቱ
1
5 በማስረዳት የፈንድ ቁጥር
ፋይና አባላትን ማበራከት
ን የድጋፍ እንክብካቤ ለኤድስ ፈንድ አባላት በቁጥር -2 2 2 11 1 11 1 ዳይሬክቶሬቱ
አገልግሎትን ማሻሻል አስፈላጊውን ድጋፍ እና 2 በደድጋፍ - --

ክትትል ማድረግ የተደረገላቸዉ
ቁጥር
ኤች.አይ.ቪበደማቸዉ 29
በቁጥር ድጋፍ ያገኙ ሰራተኞች 30 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
ላላባቸዉ የዩኒቨርስቲ ቁጥር 24 24 24 24 24 24 እና ለዳይሬክቶሬቱ
2
መምህራን ሰራተኞችና
ተማሪዎች የስነልቦና፣
የማህበራዊ፣ የህግና
የኢኮኖሚ ድጋፍ
እንዲያገኙ ማመቻቸት

በኤች.አይ .ቪ ምክንያት ድጋፍየሚደረግላቸው28 34 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች


ለተጎዱ የአካባቢው 2 በቁጥር ቁጥር 32 41 34 36 39 41 እና ለዳይሬክቶሬቱ
ህጻናት በየወሩ ድጋፍ
የሚደረግላቸው

በኤች.አይ .ቪ በደማቸው በቁጥር በሚሰጡ ስልጠናዎች ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች


ላለባቸው 1 ብዛት 24 26 - 26 - - እና ለዳይሬክቶሬቱ
የዩኒቨርስቲው
መምህራን ሰራተኞች
እና ተማሪዎች በተለያዩ
ጉዳዩች ዙሪያስልጠና
መስጠት
40 ተቋማዊአመራርን፣አመለካከትን፣አደረጃጀኤችአይቪ/ኤድስን መቆጣጠርለወጣቶች ምቹ የሆነ በቁጥር 5 የአባላዘር በሽታ 5 6 5 5 5 በ6የግቢው ባሉ ባለሙያወች
ንናአሰራሮችን ማሻሻል (Biomedical የተዋልዶ ጤና ምርመራ
intervention አገልግሎት እንዲኖር የሚሰጡ
3
ማመቻቸት ክሊኒኮች
የኤች.አይ.ቪምርመራ በቁጥር ወደምርመራ የተላኩ 45 10 25 በዳይሬከረቶሬቱ
4 እንዲሰጥ ማመቻቸት 3 ሰወች ቁጥር
0
ለክሊኒክ ሰራተኞች በቁጥር በሰለጠኑ ሰዎች ቁጥር ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
የአባላዘር በሽታዎች 17 37 - 37 - - እና ለዳይሬክቶሬቱ
3
የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስልጠና ማሰጠት

የተቋሙ ሠራተኞችን በቁጥር የተሰራጨ 25 8500 50 10000 12 2500


ኮንዶም 12 250012 2500 12 2500 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
ትኩረት ያ ያደረገ ቁጥር እና ለዳይሬክቶሬቱ
የኮንዶም ስርጭትን ማካ
3
ሄድ

ለተማሪዎችን ትኩረት ያደረገ በቁጥር የተሰራጨ 29 26800 36 3000090 7500


ኮንዶም 90 7500 90 7500 90 7500 በየግቢው ባሉ ባለሙያወች
የኮንዶም ስርጭት 4 ቁጥር
ማካሄድ

ተቋማዊ የመረጃ ማእከላትን በቁጥር ክትትል እና ድጋፍ በየግቢው ባሉ ባለሙያወች


አመራርን ማጠናከር 3 የተደረገበት ቀን 4 4 1 1 1 1
አመለካከትን
አደረጃጀትን ከአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች በቁጥር የግንኙነት ጊዜ በዳይሬከረቶሬቱ
የጸረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ - 2 - - 2 -
እና አሰራሮችን ማሻሻል
ፎረም ጋር ያለውን
2
አጋርነት በማጠናከር
መሳተፍ

የጸየጸረሱስ ክበባትን መደገፍ በቁጥር ድጋፍ የተደረገበት ግቢ ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች


እና ክትትል ማድረግ 7 7 7 7 7 7 እና ለዳይሬክቶሬቱ

3
ው በዳይሬክቶሬቱ ስር ያሉ የጸረ በቁጥር ድጋፍ የተደረገበት ግቢ ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
የኤች.አይ.ቪ ክበባትና 7 7 7 7 7 7 እና ለዳይሬክቶሬቱ
ዉ 2
ስ ማህበራትን ድጋፍና
ክትትል ማድረግ


የ 2015 በጀት ዓመት የዕቅድ 4
በቁጥር ግምገማው በተካሄደበት 2 4 11 1 1 1 1 1 በዳይሬክቶሬቱ
አፈጻጸም ግምገማ ሩብ አመት ቁጥር
አ 2
ማካሄድና የተሸሉ

ተሞክሮችን ለሌሎች
ራ ማካፈል

አሰራ
በዉጤት ተኮር ዕቅድ ላይ በቁጥር ክትትል 22
የተደረገበት 2 3 -111 1 11 1 1---- በዳይሬክቶሬቱ

የተመረኮዘ የስራ ቁጥር
ሥርዓት እንዲሰፍን
2
መደገፍ መከታተል

ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አካቶ ዘር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለሁሉም 10 10 በቁጥር በሰልጣኞች ቁጥር - 11 70 - -7 70 - በዳይሬክቶሬቱ
(Mainstreaming) መስራት አካቶ የዩኒቨርስቲዉ ክፍሎች
የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር (Mainstreaming) የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን
መፍጠርና ማጠናከር መስራት የሚያስችል የመከላከል ተግባራትን
አደረጃጀትና አሰራር እንዲያካትቱ ስልጠና
መፍጠርና ማጠናከር መስጠት
25 የት የተ/ትምህርት ጥራት፤አግባብነት እና
ኤች.አይ.ቪ/ ለአደንዛዥ እጽ በቁጥር በሰልጣኙ ቁጥር 35 500 35 600 - 35 350 -2 250- ለ- ሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
ተደራሽትን ማረጋገጥ ኤድስንለመከለከል.ኤች. ተጠቃሚ 2 እና ለዳይሬክቶሬቱ
አይ.ቪን ና በተያያዥ ተማሪዎች
ችግሮች ዙሪያ ያለዉን ተከታታይ
ግንዛቤ ማሳደግ ስልጠና መስጠት
(Beheveral ለዩኒቨርስቲዉና በቁጥር በተሳታፊ ሰዎች ቁጥር1- --- 2 2 200 --- 10 100 100 10 - በዳይሬከረቶሬቱ
intervention የአካባቢ 2
ማህበረሰብ
አደንዘዥ እጽ
ዙርያ ግንዛቤ
መፍጠር

2 ኤች.አይ.ቪን 2በቁጥር በተሰራጨ መረጃ 34 5071414 60000 17 15000 50 1500039 150003 15000ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
5
ለመከላከል እና ለዳይሬክቶሬቱ
መልክቶች የያዙ
መረጃና ስርፀት
ትምህርት(SBC
C)ማቴሪያሎችን
ማሰራጨት

የቡና ጠጡ ቶክ ሸዉ በቁጥር ፕሮግራሙ ተካሄደበት 26 በየግቢው ባለሙያወች


የሚኒ ሚዲያ እና 2 ቁጥር 6 ጊዜ 16 4
4 4 4
የስነጹሁፍ
ፕሮግራሞችን
ማመቻቸት

የተለያዩ ኩነቶችን በቁጥር ፕሮግራሙ ተካሄደበት 2 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች


ማክበር(የአለም 1 ቁጥር - 1 - - እና ለዳይሬክቶሬቱ
ኤድስ ቀን፣ የጸረ-
ሱስ ቀን…)
መማ በቁጥር 12
ፕሮግ 2 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
በዩ በግቢዎችዎች ሚኒ ራሙ 2 2 - 1 - እና ለዳይሬክቶሬቱ

ሜዲያ/የማህበረሰብ የተካ

ሬዲዮ በመደበኛነት ሄደበት
በመጠቀም በሚኒ 1 ቁጥር

ሚዲያ ዕቅድ መሰረት

የኤችአይቪ መከላከል
ትምህርቶች/መልዕክቶ
ማ በቁጥ በኩነቱ የተከናወኑ
ች እንዲያስተላልፉ
ስ 4 ር ተግባራት - 4 2 - 2 -
መከታተልና ማጠናከር



ተ የተዋልዶ ጤና በቁጥር በሰልጣኝ 22 10 12 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች
እ 22
የሜንተር ሽፕ ስልጠና 2 ቁጥር - 22 22 - -- - እና ለዳይሬክቶሬቱ
ድ መስጠት

በጊዜ ስል ስልጠናው 70 70 ለሁሉም ግቢ ባለሙያዎ ች

የአ የአቻለአቻ የተማሪዎች 2 በተሰጠበት ጊዜ -- 280 280 - - - እና ለዳይሬክቶሬቱ
የአሰልጣኞች ስልጠና -
መስጠት

የአ የአቻ-ለአቻ በቁጥር የተወያዮች ብዛት --- 43 3000 27 750 75750 50750 -7 750በየግቢው ባለሙያወች
የተማሪዎች ዉይይት 2
ማድረግ
ለ የማሪዎች እና ሰራተኞች በቁጥር በ የሳታፊ ቁጥር 32 344 17 600 85 45 100 25 10020 በየግቢው ባለሙያወች
የእህቶች ለእህቶች 2 200 200
ዉይይቶችን ማካሄድ

የአካል 2 ቁጥር ሰልጣኝ ቁጥር - 20 - - ለሁሉም ግቢ


ጉዳተኞች 20 20 ባለሙያዎ ች እና
በኤች.አይ. ለዳይሬክቶሬቱ
ቪ/ኤድስ
ዙሪያ
ስልጠና
መስተት

የተሸለ ተሞክሮ የተሄደበት 2 1 - - 1


ካላቸዉ 2 ቁጥር ቁጥር ---
ኒቨርሲቲዎ
ች ጋር
የልምድ
ልዉዉጥ
ማድረግ
እቅዱ ያዘጋጀዉ እቅዱን ያጸደቀዉ

ሲ/ር ምህረት ጌታቸዉ

ፊርማ -------------

ቀን---------------------

Common questions

Powered by AI

Economic factors in the Directorate’s approach involve securing financial resources, managing assets efficiently, and engaging in fundraising activities to support HIV/AIDS management and prevention programs. The focus is on financial sustainability to maintain and expand health interventions and support services .

The university's efforts to foster institutional leadership and reform include enhancing organizational structures and processes, promoting leadership capacity through targeted training, and implementing strategic initiatives aimed at improving management practices and accountability .

Stakeholder collaboration is emphasized as critical for implementing HIV/AIDS interventions, as it fosters resource sharing, enhances program reach, and ensures comprehensive support systems are available for affected individuals. Collaboration with government and non-governmental organizations helps integrate efforts and leverage expertise and funding .

The main challenges anticipated included low community engagement regarding HIV/AIDS issues, inadequate funding, and lack of necessary tools for training and education. The Directorate planned to overcome these by enhancing awareness programs, seeking financial support through partnerships, and employing diverse educational tools such as multimedia to engage communities effectively .

Bahir Dar University aims to support its HIV/AIDS-affected students and staff by offering psychological, social, legal, and economic support, as well as integrating health services with educational and administrative support systems to foster a supportive and inclusive environment .

The Directorate intends to improve education quality by ensuring teaching relevance and adaptability, enhancing curriculum standards, and providing continuous training for educators. This holistic approach is designed to make educational offerings more aligned with both national needs and international standards .

The document describes a strategic alignment where the university's strategic plan is crafted to complement Ethiopia’s national strategy on HIV/AIDS. This involves adopting shared objectives and methods, thereby ensuring the university’s efforts contribute effectively to the national goals of prevention and control .

The document proposes integrating academic and administrative sectors by mainstreaming HIV/AIDS strategies across the university, involving faculties in awareness and education programs, and ensuring that administrative policies support the health and safety of the university community through enhanced coordination and communication .

The SWOT analysis identified key strengths such as established resources and support systems, while key weaknesses included limitations in resource acquisition and management. Opportunities involved potential partnerships and technological advancements, whereas threats included external economic and social pressures .

Bahir Dar University's Directorate plans to address the challenges in managing HIV/AIDS by aligning and integrating the university's goals with the national strategic plan outlined for 2021-2025. This involves enhancing their own strategies for prevention and control, strengthening stakeholder collaboration, and focusing on effective interventions like biomedical and behavioral strategies .

You might also like